ሚያዚያ
23, 1998
ለእስልምና
ጉዳዮች
ጠቅላይ
ጽ/ቤት
አዲስ
አበባ
ኢትዮጵያ
ትክክለኛው
ምክንያት
ግልፅ ያልሆነው
በቅርቡ
በአገራችን
ቅዱስ
ቁርዓኑን
ባልሆነና
ባልተገባ ቦታ
በአፀያፊ
መልኩ በመጠቀም
የተከሰተው
ድርጊት አሳዛኝና
አሳፋሪ
ከመሆኑም
በላይ
ፍትሃዊ
መልስ
ሊሰጥበት
የሚገባ
አጣዳፊ
ጉዳይ
ነው።
በወሎ
ከሚሴ
እንደዚሁም
በኢትዮጵያ
የከፍተኛ ትምህርት
ተቋማት
በአዋሳ
ደቡብ
ዩኒቨርሲቲ፣
በአዲስ
አበባ
ዩኒቨርሲቲና
ቀጥሎም በጅማ
ዩኒቨርሲቲ
የደረሰዉ የቁርዓንንና
የነቢዩ
ሙሐመድን
(የአላህ
ሰላምና
በረከት
በእርሳቸው
ላይ
ይዉረድ)
ማንነት
ለማራከስ
የተደረገዉ
ሙከራ ከአፀያፊና
አሳፋሪነት
ባሻገር ድርጊቱ
ከሰፊው
የኢትዮጵዊያ
ሕዝብ
የረጅም
ጊዜ
አብሮ
የመኖርና
የመቻቻል ሕይወት
ታሪክ
ጋር
አብሮ
የማይሄድ
ነው።
ምንም
እንኳን
ድርጊቱ
የጥቂት
ተንኮለኞች
ጉዳይ
መሆኑን
መገመት
ቢቻልም
እነዚህ
ተንኮለኞች
አገር
አጥፊ
ድርጊታቸውም
ሆነ ምኞታቸው
ሥር
እንዳይሰድ
በአፋጣኝ
ለፍርድ ቀርበው
ተገቢ
እርምጃ
ሊወሰድባቸው
ይገባል። የተደረገው
ድርጊት
የኢትዮጵዊያን
ሙስሊሞችን
ስነ-ልቦና የሚጎዳ
ብቻ
ሳይሆን
በመላው
ዓለም
የሚኖሩትን
ከ1.5 ቢሊዮን
በላይ
የሚቆጠሩ
ሙስሊሞችን ሰሜት የሚነካ
መሆኑ
ጉዳዮን
አሳሳቢ
ያደርገዋል።
ኢትዮጵያ
ሀገራችን
በቀያቸው የእምነት
ነፃነትን
በመነፈጋቸው የእምነትን ከለላ የፈለጉ
የሙስሊም
ስደተኞችን ተቀብላ ያስተናገደች
የመጀመሪያዋ
የስደት/የሂጅራ
አገር
(the land of First Hijra)፤ በጊዜው ከመካ
ቀጥሎ
እስልምና
የተሰበከባት
በዓለም የመጀመሪያዋ
ሀገር
ነች።
ታድያ
ይህ
አኩሪ
ታሪካችን
በማንኛውም
ኢትዮጵያዊ ዘንድ መዘንጋት
ይቅርና
ችላ
ሊባልም
የሚገባዉ
ነገር
አይደለም።
ከዚህም
አንፃር
አሁን
የደረሰው
ሁኔታ
ለዚህ
ተቻችሎ
ለኖረ
ሕዝብ
ሊያሳስበዉ፤
ሊያስጨንቀውና
ሊያስቆጨው
ይገባል።
የተወሰኑ
ክፍሎች
ይኽን
ሀቅ
ከተጨባጩ
የሕዝብ
አብሮ
የመኖር
ፍቅር
በመነጠል
ለዕኩይ ዓላማቸው
መተግበሪያ
ሊያውሉት መሞከር
ፋይዳ
የማይኖረው
ከንቱ
ልፋት
መሆኑን
ከታሪክ
ሊማሩ
ይገባቸዋል።
እኛ
ኢትዮጵያዊያን
ሙስሊሞችና
ክርስቲያኖች ቁርዓን አህሉል-ኪታብ
ብሎ
የሚጠራን
የመጽሐፍ
ሰዎች ቤተሰብ
ነን።
ሀገራችን
ኢትዮጵያ
ዛሬ ካለችበት
ዉስብስብ
ችግርና የድህነት
ቀንበር
ልትወጣ
የምትችለው
በሕዝቦቿ መካከል
በመከባበርና
በመግባባት ላይ የተመሰረተ
ሰላም
ሲኖር
ብቻ
ነው።
ለዚህም
እገሌ
ከእገሌ
ሣንል
የባህላችን
አንድ ገጽታ
የሆነዉን
መከባበርና መቻቻል ምርኩዝ
አድርገን
ጠንክረን መያዝና
ለገቢራዊነቱም
በርትተን
መስራት ይጠበቅብናል።
በዚህ
አጋጣሚ
ለመላው
ኢትዮጵያዊን
ሙስሊም ወገኖቼ
የተሰማኝን
ጥልቅ ሀዘን
እገልጻለሁ።
ይህ አሳፋሪ
ጉዳይም
በአስቸኳይ
በሚመለከተው
ክፍል ተጣርቶ
ጥፋተኞች
ለፍርድ እንዲቀርቡ፤
አስፈላጊና
የማያዳግምም ቅጣት እንዲሰጣቸው
እጠይቃለሁ።
ሰላም ለኢትዮጵያ
ሕዝብ!
ከዶ/ር
ልጅ
አስፋ-ወሰን
አስራተ-ካሳ
ፍራንክፈርት
ጀርመን