NEME - your only gateway to info. on Islam in Ethiopia and Ethiopian Muslims

O mankind! We created you from male and female, and made you into nations and tribes, so that you may come to know one another. Truly, the most honoured of you in God's sight is the greatest of you in piety. God is All-Knowing, All-Aware. (Qur'an, 49:13)

 
 
 
 Event:- Online Lecture - at 21:00 cet.
WWW NEME
Bilal ul-Habasha
Ethiopian Muslims Community Platform

በበድር ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ፌደሬሽን አባል ድርጅቶችና የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰቦች በአዉሮፓ እና ሳዑዲ-አረቢያ

ሰሞኑን በአዲስ አባባ የፋጢመቱ-ዛህራ (አራዳ/አራት ኪሎ) መስጂድ መፍረስንና ህገ-መንግሰታዊ መብቶቻቸዉን ለማስከበር ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በወጡ ሙስሊም ዜጎች ላይ የፌዴራል ፖሊስ ስለአደረሰዉ የማቁሰል አደጋና የጅምላ እስራትእንዲሁም በተደጋጋሚ በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለዉን በደልከጊዜ ወደጊዜም እየተባባሰ የመጣዉን ጠቃላይ የፀረ-ኢስላም ፀረ-ሙስሊም እንቅስቃሴና የፀብ አጫሪነት ጉዳይ አስመልክቶ የተሰጠ የአቋም መግለጫ

 

አገራችን ኢትዮጵያን በታሪክ ቀደምት ቦታን ከሚያሰጡዋት ታሪካዊ አውነታዎች አንዱ ከመካ የተሰደዱ ሙስሊሞች እርሱ ዘንድ ማንም አይበደልም ተብሎ በተነገረለት የወቅቱ የኢትዮጵያ መንግስት ዘንድ አስተማማኝ የኑሮ ዋስትና እንደሚያገኙ በማመን በነብያቸው ተልከው በሰላም ወደ ሀገረ ኢትዮጵያ መግባትና ለረጅም ዘመናትም ሙስሊም ካልሆኑ የህብረተሰቡ ክፍሎች ጋር በሰላም አብረው መኖር መቻላቸው ነውበጊዜው የነበሩት የአክሱም ንጉስም  (ነጃሽ አስሐማ) ለሙስሊም ስደተኞች ጋሻና መከታ  የነበሩ በመሆናቸው በመላው የዓለም ሙስሊም ህብረተሰብ ስነ ልቦና ውስጥ ህያው ሆኖ የሚኖርና የእኛ ኢትዮጵያዊያኖችም አንዱ አኩሪ ገድላችን ነውባላቸው እምነት እና የፖለቲካ ልዩነት ሀገር ለቀው ለተሰደዱ ህዝቦችም የጭንቅ ቀን ጋሻና መከታ በመሆንና ተገን በመስጠት ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሀገር በመሆኗ ሀገራችን በዓለም ህዝቦች ዘንድ በምሳሌነት ለዘለዓለም ስትጠቀስ ትኖራለች

ነገር ግን ይህ አብሮ የመኖር መርህ ተዘንግቶ በተለይም12ኛው ክ/ዘመን መገባደጃ ጀምሮ በሙስሊሞች ስቃይና መከራ ተተክቷልየክርስትና  ሃይማኖት መንግሰታዊ ይዞታ ያለዉና የሌሎች የበላይ ሲደረግሎች ደግሞ መጤ እና  በሁለተኛ ደረጃ እንዲታዩ ተደርገዋልይህም በታሪካችን ላይ ዘለዓለም የሚኖርና ጎልቶ የሚታይ ጠባሳን ጥሎ አልፋል 

የንጉሥ ኃይለ-ስላሴ የአገዛዝ ስርዓት ከከሰመ በኋላ የክርስትና የመንግሰት ሀይማኖታዊነት እየቀነሰ ቢመጣምየአንዳንድ ግለሰቦችና ድርጅቶች እኩይ እምነትና ተግባር  ብዙም አልተለወጠምበተለያዩ የመንግስት መዋቅሮችና በሕዝብ ተቋሞች የሚሰሩ  ሃላፊነት የጎደላቸው ግለሰቦችም ለዕኩልነትና ለመብት እንደዚሁም ሰለ ህገ-መንግስታዊ የእምነት ነጻነት ያላቸዉ ግንዛቤ እጅግ ጠባብ መሆኑ ግልፅ እየሆነ መጥቷልእኒህም  እኩይ አስተሳሰብ የተጠናወታቸዉ ዜጎችና ተቋሞች በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለሙስሊሞች ያላቸውን ድብቅ ጥላቻ ለማሳየት የማይሸርቡት ሴራ የማይፈነቅሉት ድንጋይ አልተገኘምናየታሪክ ጠባሳ የመዳን እድል ተነፍጎት ይገኛል 

ከሰሞኑም በአራዳ ክፍለ ከተማ በቀበሌ 07/17 ከሁለተኛ ፖሊሰ ጣቢያ በሰተጀርባ የሚገኘዉ የፋጢመቱ-ዛህራ (አራዳ/አራት ኪሎ) መስጂድ መፍረስም በታሪካችን አሳፋሪ ጥቁር ነጥብ ከምንለዉ ዉስጥ የሚካተት ሆኗል

በእንቅርት ላይ ጆሮ ገድፍ እንዲሉ ለባለፉት ስድስት ወራት ብቻ፡-

o       በወሎ-ከሚሴ በነብያችን (ሱ.ዐ.ወ) ላይ የሥም ማጉደፍ ዘመቻ ሲደረግ

o       በአዋሳበአዲስ አበባበጅማ ዩኒቨርስቲዎች እና በሌሎችም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተፈጸመው ቁርአንን የማራከስ ድርጊትእጅ-ከፍንጅ የተያዘው ግለሰብም ካለምንም ቅጣት በነጻ መለቀቁና ይህም ተመሳሳይ ድርጊቶች እንዲከሰቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉ 

o       በጅጅጋ ንብረትነቱ የአንድ ክርስቲያን በሆነ ድርጅት ቁርዓን ለሽያጭ እቃ መጠቅለያ ሲደረግ

o       በአላጌ ኮሌጅ በሙስሊም ተማሪዎች ላይ የደረሰው ተደጋጋሚ ድብደባና እስራት

o       በጎንደር130 አመት በላይ የሆነው የሙስሊሞች የመቃብር ቦታ ለግል ባለሀብት ሲሰጥ

o       በጂማ ዞን በመስጊዳችን ላይ ጥቃት ሲደርስና ሌሎችም የሙስሊሙን የእምነት ነፃነት የሚጋፉና ማነንቱንም የሚፈታተኑ ድርጊቶች ሲከሰቱ

o       ሀገ-መንግስቱ የሰጠውን የሀይማኖት ያለ ምንም ተጽኖ የመተግበር ነጻነት በሚጻረር መልኩ የተለያዩ ትምህርት ቤቶችና ተቋማት ሙስሊም እህቶቻችንና ልጆቻችን ሂጃብ እንዳይለብሱ በመከልከል የእምነት ግዴታቸዉን ለመወጣት በሚያደርጉት ጥረት ላይ ማዕቀቦች ሲደረጉባቸው

በመንግስት በኩል በዝምታ መታለፋቸውና የተወሰዱ አዎንታዊ እርምጃዎችም ባለመኖራቸው በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ ታላቅ ቅሬታ እየፈጠሩና ትእግስታቸውን እየተፈታተኑ ይገኛሉታድያ እነዚህና መሰል ክስተቶች ልዩ ትኩረት ተችሯቸው አጥፊዎች ለህግ እየቀረቡ ተገቢውን ቅጣት በማግኘት ችግሩ በአጭር እንዲቀጭ ካልተደረገ ሃገሪቷ ከማትወጣበት ቀውስ ውስጥ እንድትገባ አስተዋጽኦ ማድረጉ አይቀሬ ነው

ከዚህም ባሻገር የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ጥያቄ ያላጤነና ሙስሊሞችን ያላሳተፈ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴም ሆነ የሀገር ግንባታ ማሰብ በአንድ እጅ ለማጨብጨብ  እንደመሞከር ይሆናልየሃገሪቱንም እድገት አንድ እርምጃ ወደፊት ሁለት እርምጃ ወደኋላ ከማራመድ ሌላ እድል ሊኖረው አይችልምለሃገራችን ወደኋላ መቅረት ምክንያት ከሆኑት አንዱ እና ዋናው ነጥብ ሙስሊሞች በሃገራቸው ጉዳይ የሚጫወቱት ሚና በረቀቀ ዘዴ ውሱን እንዲሆን መደረጉ ነውም ብለን እናምናለንሙስሊሙን እንደ ሁለተኛ ዜጋ የማየት መንፈስ የተጠናወታቸው አንዳንድ ግለሰቦችና ተቋማት ኢትዮጵያ አድጋ እና በልፅጋ የዜጎቿ እኩል እናት ሆና ለማየት እንደማይመኙ በተደጋጋሚ ከሚከስቱ ድርጊቶች ለመገንዘብም ችለናል 

በህዝቦች መካከል እኩልነት ሲጠፋና አንዱ ወገን የሌላውን መብት ሲገፍ ዜጎች ህጋዊ እና ሰብዓዊ መብቶቻቸውን ለማስከበር አስፈላጊውን እርምጃ መውሰዳቸው አይቀሬ ነውለዚህም ዛሬ ስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት ሕያው ማስረጃ ይመስለናልይህን ሃቅ የሚያውቅ መንግስት አሁን የሙስሊሞች መብት ሃላፊነት በጎደላቸው ባለስልጣናትና የሃይማኖት መሪዎች ሲጣስ  የእርስ በእርስ ግጭት እንዲፈጠር በሚፈልጉ ግለሰቦች ሲደፈር እያየ እርምጃ አለመውሰዱ በጣም አሳዝኖናልአሳስቦናልም 

እንደደረሰን ዜና ከሆነ (በነሀሴ 11, 1998 በአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የተሰጠ መግለጫ) ለመስጂድ መስሪያ ይዉል ዘንድ መንግስት ለሙስሊሞች በአፍንጮ በር አካባቢ 2230 ካ.ሜ. ቦታ መስጠቱ በወቅቱ የተከሰተውን ውጥረት ከማርገብና የሙስሊሙንም የፀሎት ቦታ ጥያቄ ከማሟላት ረገድ የተወሰደ እርምጃ ከሆነ መንግስትን የሚያስመሰግን ድርጊት ነው እንላለንከዚሁም ጋር ግን  የችግሩ ቁልፍ የሆነው የአራዳ መስጂድ ጉዳይ ተድበስብሶ መታለፍ የማይገባዉና መስጂዱ በማን ትእዛዝ እና  ለምን እንደፈረሰ መጣራት ያለበት ጉዳይም እንደሆነ እናምናለን

ከዚህ አንጻር በድር ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ፌደሬሽን አባል ድርጅቶችና በአዉሮፓ  እና በሳዑዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያን  ሙስሊሞች ማህበረስቦች ገሪቱ ህገ-መንግስት የሰጠዉ የእምነት ነፃነት ተግባር ላይ ይዉል ዘንድ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ስናቀርብ መንግስትም ለጥያቄዎቻችን ተገቢዉን ትኩረት ሰጥቶ አስቸኳይ መልስ እንደሚስጠንና ከላይ ለመዘርዘር ለሞከርናቸውና መስል ችግሮችም ዘላቂ መፍትሄ እንደሚያደርግ በማመን ነዉ 

ሀ)   25 አመት በላይ ግልጋሎት ላይ የነበረዉን የፋጢመቱ-ዛህራ (አራዳ/አራት ኪሎ) መስጂድ አላግባብ እንዲፈርስ የወሰኑ ባለስልጣኖች ለፍርድ እንዲቀርቡመስጂዱም በቦታው ላሉ ሙስሊሞች ያገለግል ዘንድ ከድሮ ቦታው እንዲገነባመስጂዱ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በሀይል እንድፈርስ ተደርጎ ቦታው የይገባኛል ጥያቄ ስላለበት ጉዳዩ በፍርድ ቤት ይታያል የሚለው በተከታታይ ያየነው በመሆኑ የይገባኛል ጥያቄው መስጂዱ እንደነበር ከተሰራ በኋላ መስተናገድ ይገባዋል እንላለን

ለ)   የመስዱን ከህግ ብይን ዉጭ መፍረስ ተከትሎ በሙስሊሞች ላይ ለደረሰው የንብረትና የሞራል ጥፋት እንደዚሁም የአካል ጉዳት ካሳ እንዲከፈል

ሐ)   የመስጂዱን ያለአግባብ መፍረስ በመቃወም ቅሬታቸዉን በስላማዊ መንገድ በመግለጽ ላይ እያሉ የታሰሩ ሙስሊሞች ሙሉ በሙሉ በአስቸኳይ እንዲፈቱ

መ)   የፌዴራል ፖሊስ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የወሰደዉ ዕርምጃ በአስቸኳይ እንዲጣራ

ሠ)   በአንዳንድ የቤተክርስቲያን ሃላፊዎች እና መንፈሳዊ ድርጅቶች በሙስሊሞች ጉዳይ ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት እንዲያቆሙ እና በኢስላማዊ ተቋማት ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የማዘዝ ስልጣን የሌላቸው መሆኑን እንዲገነዘቡ መንግስት ምክር እንዲሰጣቸው

ረ)   ለወደፊት ይህን መሰል ድርጊት እንዳይደገምና ዜጎች ሰለ ዕምነት ነፃነትና ሰለህዝቦች እኩልነት የተስተካከለ ግንዛቤ እንዲኖራቸዉ መንግስት ከአንደኛ  ደረጃ ት/ቤቶች እስከ ከፍተኛ ተቋማት ድረስ በትምህርት መርሃ ግብር ዉስጥ የተካተተ ስልጠና (sensitivity training) እንዲያደርግ ለማሳሰብ እንወዳለን   

ከዚሁም ጋር የአዲስ አበባ ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን መብታቸዉን ለማስከበር የወሰዱትን ሰላማዊ እርምጃ ሙሉ በሙሉ እንደምንደግፈው እየገለጽን የሐይማኖት ነጻነትየመብትና የፍትህ ጥያቄዎቻችንም ሙሉ በሙሉ እስኪመለሱ ድረስ ህጋዊ መንገዶችን በመከተል ትግላችንን እንቀጥላለንበዚሁ አጋጣሚም ሙስሊሙ ወገናችን በስሞኑ የውሃ መጥለቅለቅ የተጎዱ ወገኖቻችንን በመርዳቱ ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን 

ሰላም እና ብልጽግና ለሃገራችን እንመኛለን!!!

 

በድር ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ፌደሬሽን አባል ድርጅቶች
በአዉሮፓና በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያዊያን  ሙስሊሞች ማህበረስቦች
21-8-2006

Online - Activity
20/01/06
Lecture
Dawa & Da'iyah
(Sh. Adem Kamil)
23/12/05
Lect. + Q&A
(Sh. Adem Kamil)
Radio Negashi (Stockholm, Sweden)
Radio First Hijra
(Washington DC.)
Week of

Latest
U P L O A D

O N L I N E
L e c t u r e s

Next Lecture'll be on at kemishitu 4:00 se'at (Ethio)/ 21:00 cet/ 10:00 pm Mekka, Insha Allah. Learn more

- More Audio
- Ask the Scholar


Subscribe to the NEME egroup


Your are visitor

since 28/02/2004!

Network of Ethiopian Muslims in Europe, NEME © 2004-2005 All Right Reserved.
NEME has no the policy of editing or rejecting to publish the views of any participant, unless it incites hatred and the like, be it against individuals or groups. In that case, NEME deserves the right to deny space for such opinions in its site. NEME would like to remind all those who wish to make use of our service thus that we stand for understanding, respect and unity of the Muslim umma, and not for hatred, division, or sectorianism of any sort - all these are abhorred by the Amighty Allah (sw) and His final and beloved Prophet (saw). NEME promotes tolerance and peaceful co-existence of Ethiopians of all faith.

Views and opinions expressed in the articles we publish are that of the contributer(s) and do not necessarily reflect the position of NEME.