NEME - your only gateway to info. on Islam in Ethiopia and Ethiopian Muslims

O mankind! We created you from male and female, and made you into nations and tribes, so that you may come to know one another. Truly, the most honoured of you in God's sight is the greatest of you in piety. God is All-Knowing, All-Aware. (Qur'an, 49:13)

 
 
 
 Event:- Online Lecture - at 21:00 cet.
WWW NEME
Bilal ul-Habasha
Ethiopian Muslims Community Platform
NOTE: You need to have Unicode Geez font installed on your PC to read the article below. Please click for a PDF version of the text.

በሃገራችን በቅዱስ ቁርዓን ላይ የተፈፀመውን ፀረ ኢስላም ወንጀል አስመልክቶ ከነጃሺ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ማህበር በስዊድን የተሰጠ መግለጫ

ቢስሚላሂ አረህማን አረሁም

በሃገራችን ታላላቅ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ቅዱስ ቁርዓንን ለሽንት ቤት መፀዳጃነት በመጠቀም የተፈፀመውን እጅግ በጣም አሳፋሪ የሆነ ፀረ ኢስላም ወንጀል የሰማነው ጥልቅ በሆነ ሃዘንና ምሬት ነው።

በሙስሊሞች ዘንድ ቅዱስ ቁርዓን ያለው ቦታ ከምንም ነገር በላይ ከፍ ያለ ነው። ቅዱስ ቁርዓን የሰው ልጆች ቀጥተኛ ወደሆነው ጎዳና ይመሩ ዘንድ ከፈጣሪያችን አላህ ለነብዮ መሃመድ የተገለጸ የምህረት ቃል ነው። በዚህም የተነሳ ሙስሊሙች የሰውነታቸውን የተለያዩ ክፍሎች በውሃ ካላጠሩ ወይንም ውዱዕ ካላደረጉ በስተቀር አይነኩትም። ለዚህም ነው ቅዱስ ቁርዓን ላይ የተፈፀመው ወንጀል በሙስሊሙች ዘንድ ለአስከፊነቱ ወደር የማይገኝለት። ኢትዮጵያ  ሙስሊሞችና የሌሎች እምነት ተከታዮች ጎን ለጎን በመሆን ለረጂም ዘመናት የኖሩባት ሃገር ናት። በእስልምናና ክርስትና እምነት ተከታዮች መካከል የነበሩት ግንኙነቶች ሁልጊዜ በእኩልነትና በመቻቻል ላይ የተመሰረቱ ነበሩ ብሎ ለመናገር አይቻልም። ለዚህም በርካታ የታሪክ መረጃዎችን መጥቀስ ይቻላል። ከአፄዎቹ ስርአት መደምሰስ ወዲህ ግን ሁኔታዎች የመሻሻል አዝማሚያ አሳይተውል ማለት ስህተት አይሆንም። ያም ሆኖ ግን በተለይ በአሁኑ አለማችን ላይ በሃይማኖቶች ግጭት ሳቢያ ብዙ ደም በሚፈስበት ወቅት እንዲህ ያለው የሃገሪቱ ግማሽ አካል የሁነውን የሙስሊሙን ልብ ክፉኛ ያቆሰለና ሌሎች ሠላም ወዳድ ዜጎችን ያሳዘነ ፀረ ኢስላም ወንጀል መፈፀሙ ሃገሪቱን ወደ ከፋ ችግር ውስጥ ሊጨምራት እንደሚችል መገመት አዳጋች አይሆንም።

ነጃሺ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ማህበር በስዊደን የተቋቋመበት አላማ በስዊደን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የሃይማኖታቸውንና የባህሎቻቸውን እሴቶች ሳይለቁ ከቀሪው ህብረተሰብ ጋር በጋራ የሚኖሩበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ነው። ለሃገራችን ኢትዮጵያ ሠላም ፣ እድገትና ብልጽግናም እንዲሁ  የበኩላቸውን አወንታዊ አስተዋፅዖ የሚያደርጉበትን መንገድ ይከፍታል። ከዚህ መንፈስ በመነሳት በቅዱስ ቁርዓናችን ላይ በተሰነዘረው አፀያፊ ፀረ ኢስላም ወንጀል ሣቢያ ሃገራችን ላይ ያጠለለው የጥፋት ደመና ይገፈፍ ዘንድ ፍላጎታችንም የምንታገልለትም አላማ ነው። ይህም ትግላችን ይሰምር ዘንድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ጥያቄዎቻችንን ምላሽ እንዲያገኙ የኢትዮጵያን መንግስት እንጠይቃለን።

1.    ለወንጀሉ ተጠያቂ የሆኑት ግለሰቦች ለፍርድ ቀርበው ለጥፋታቸው ተመጣጣኝ የሆነ ቅጣትን እንዲቀበሉ

2.    ወንጀሉን ከፈፀሙት ግለሰቦች ጀርባ ሊኖር የሚችለው የተቀነባበረ ሴራ እንዲመረመርና ግልጽ እንዲደረግ

3.    ተመሳሳይ ወንጀሎች በድጋሚ እንዳይፈጸሙ አስፈላጊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ።

ይህ በሃገራችን ብሄራዊ ደህንነት ላይና በተለይ ደግሞ በሙስሊሞች ላይ የተሰነዘረው አፀያፊ ፀረ ኢስላም ወንጀል ከፍተኛ እንደመሆኑ መጠን የሚያስከትለውም መዘዝ የዚያኑ ያህል ከፍተኛና ዘላቂ ሊሆን የሚችል ነው። ይህንንም ከግምት ውስጥ በማስገባት መንግስት ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረትን በመስጠት  ፀረ ኢስላም ወንጀል በሃገሪቱ ህገ መንግስትም ሆነ በስልጣን ላይ ባለው ፓርቲ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በማሳየት በወንጀሉ ሳቢያ ሊከተሉ የሚችሉ የአጭርና የረጅም ጊዜ መዘዞችን እንዲከላከል እናሳስባለን።

በፍትህና በመብት እኩልነት ላይ የተመሰረተች የበለፀገች ሰላማዊት ኢትዮጵያን

ለመመሥረት ባንድነት እንነሳ! 

የነጃሺ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ማህበር በስዊድን

የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ

Online - Activity
20/01/06
Lecture
Dawa & Da'iyah
(Sh. Adem Kamil)
23/12/05
Lect. + Q&A
(Sh. Adem Kamil)
Radio Negashi (Stockholm, Sweden)
Radio First Hijra
(Washington DC.)
Week of

Latest
U P L O A D

O N L I N E
L e c t u r e s

Next Lecture'll be on at kemishitu 4:00 se'at (Ethio)/ 21:00 cet/ 10:00 pm Mekka, Insha Allah. Learn more

- More Audio
- Ask the Scholar


Subscribe to the NEME egroup


Your are visitor

since 28/02/2004!

Network of Ethiopian Muslims in Europe, NEME © 2004-2005 All Right Reserved.
NEME has no the policy of editing or rejecting to publish the views of any participant, unless it incites hatred and the like, be it against individuals or groups. In that case, NEME deserves the right to deny space for such opinions in its site. NEME would like to remind all those who wish to make use of our service thus that we stand for understanding, respect and unity of the Muslim umma, and not for hatred, division, or sectorianism of any sort - all these are abhorred by the Amighty Allah (sw) and His final and beloved Prophet (saw). NEME promotes tolerance and peaceful co-existence of Ethiopians of all faith.

Views and opinions expressed in the articles we publish are that of the contributer(s) and do not necessarily reflect the position of NEME.