Network of Ethiopian Muslims

አቶ ኤልያስ ሬድማን በ80 ሚሊዮን ብር እንደሚጠየቅ ተጠቆመ PDF Print E-mail
Thursday, 21 January 2010 14:39

Ethiopia Zare (ረቡዕ ታህሳስ 28 ቀን 2002 ዓ.ም. January 6, 2010)

የኢትዮጵያ እስልምና ጉባዔ ጠቅላይ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት የነበረውና ባለፈው ዓመት ከሥልጣን የተነሳው አቶ ኤልያስ ሬድማን በ80 ሚሊዮን ብር እንደሚጠየቅ ተጠቆመ።
 
“ለአልፋ ሕንፃ ግዢ” በ17 ሚሊዮን ብር ክስ ተመስርቶበት የነበረው አቶ ኤልያስ ሬድማንና ግበረ አበሮቹ የምዝበራው መጠን ወደ 80 ሚሊዮን ብር ማደጉን የገለጹት የምክር ቤቱ ምንጮች፤ ግለሰቡ በኢህአዲግ አባልነቱና በሥልጣኑ ተጠቅሞ በርካታ ንብረቶችን አፍርቷል። በቤተሰቦቹም ስም አከፋፍሎታል ብለዋል።
 
አቶ ኤልያስ የ1997 ዓ.ም. ምርጫን ተከትሎ ኢህአዲግ በወሰደው እርምጃ አጣሪ ኮሚሽን በተቋቋመበት ወቅት የኮሚሽኑ አባል በመሆን ወታደሮቹ በህዝቡ ላይ የወሰዱትን እርምጃ “ተገቢ ነበር” ብለው ከፈረዱ ሁለት ግለሰቦች አንዱ መሆኑ ይታወሳል።

Comments
Add New Search RSS
+/-
Write comment
Name:
Email:
 
Website:
Title:
UBBCode:
[b] [i] [u] [url] [quote] [code] [img] 
 
 
Please input the anti-spam code that you can read in the image.

3.26 Copyright (C) 2008 Compojoom.com / Copyright (C) 2007 Alain Georgette / Copyright (C) 2006 Frantisek Hliva. All rights reserved."

 
Rmadhan Mubarak
Copyright © 2010 Network of Ethiopian Muslims. All Rights Reserved.
Joomla! is Free Software released under the GNU/GPL License.