Ramadhan Reminder, 11.09.1427

In the Name of Allah, the Merciful, the Compassionate


In the Name of Allah, the Merciful, the Compassionate

Q009:111
Surely Allah has bought of the believers their persons and their property for this, that they shall have the garden; they fight in Allah's way, so they slay and are slain; a promise which is binding on Him in the Taurat and the Injeel and the Quran; and who is more faithful to his covenant than Allah? Rejoice therefore in the pledge which you have made; and that is the mighty achievement.

Q010:009-010
Those who believe, and work righteousness,- their Lord will guide them because of their faith: beneath them will flow rivers in gardens of bliss.

Their prayer therein will be: Glory be to Thee, O Allah! and their greeting therein will be: Peace. And the conclusion of their prayer will be: Praise be to Allah, Lord of the Worlds!

 

Q010:057
O men! there has come to you indeed an admonition from your Lord and a healing for what is in the breasts and a guidance and a mercy for the believers.

 

Q010:104-107
Say: O people! if you are in doubt as to my religion, then (know that) I do not serve those whom you serve besides Allah but I do serve Allah, Who will cause you to die, and I am commanded that I should be of the believers.

And that you should keep your course towards the religion uprightly; and you should not be of the polytheists.

And do not call besides Allah on that which can neither benefit you nor harm you, for if you do then surely you will in that case be of the unjust.

And if Allah should afflict you with harm, then there is none to remove it but He; and if He intends good to you there is none to repel His grace; He brings it to whom He pleases of His servants; and He is the Forgiving, the Merciful.

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩኅ በጣም አዛኝ በኾነው

ቁ.009፡111
አላህ ከምእምናን ነፍሶቻቸውንና ገንዘቦቻቸዉን ገነት ለነሱ ብቻ ያላቸው በመኾን ገዛቸው፤ በአላህ መንገድ ላይ ይጋደላሉ፤ ይገድላሉም፤ ይገደላሉም፤ በተዉራት፣ በኢንጂልና በቁርአንም (የተነገረዉን) ተስፋ በርሱ ላይ አረጋገጠ፤ ከአላህም የበለጠ በኪዳኑ የሚሞላ ማነው?
በዚያም በርሱ በተሻሻጣችሁበት ሽያጫችሁ ተደሰቱ፤ ይህም እርሱ ታላቅ ዕድል ነው።

ቁ.010፡009-010
እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ጌታቸው በእምነታቸው ምክኒያት (የገነትን መንገድ) ይመራቸዋል፤ ከሥሮቻቸው ወንዞች ይፈስሳሉ፤ በመጠቀሚያ ገነቶች ዉስጥ ይኖራሉ።

በርሷም ዉስጥ ጸሎታቸው፦ ጌታችን ሆይ! ጥራት ይገባህ (ማለት ነው)፤ በርሷ ዉስጥ መከባበሪያቸዉም ሰላም መባባል ነው፤ የመጨረሻ ጸሎታቸውም ምስጋና ለዓለማት ጌታ ይኹን (ማለት) ነው።

ቁ.010፡057-058
እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሣጼ፣ በደረቶች ዉስጥም ላለው (የመጠራጠር በሽታ) መድኅኒት፣ ለምእምናንም ብርሃንና እዝነት በእርግጥ መጣላችላችሁ። በአላህ ችሮታና በእዝነቱ (ይደሰቱ) በዚህም ምክንያት ይደሰቱ፤ እርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው በላቸው።

ቁ.010፡104-107
እናንተ ሰዎች ሆይ! ከኔ ሃይማኖት በመጠራጠር ውስጥ ብትኾኑ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን አልገዛም፣ ግን ያንን የሚገድላችሁን አላህን እግገዛለሁ፤ ከምእምናን እንድኾንም ታዝዣለሁ በላቸው።

ፊትህንም (ወደ ቀጥታ) ያዘነበልክ ስትኾን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፤ ከአጋሪዎችም አትሁን።

ከአላህም በቀር የማይጠቅምንና የማይጎዳን አትግገዛ፤ ብትሠራም አንተ ያንጊዜ ከበደለኞች ትኾናለህ፣ (ተብያለሁ በላቸው)።

አላህም ጉዳት ቢያደርስብህ ከርሱ ሌላ ለርሱ ገላጭ የለዉም፤ በግጎንም ነገር ቢሻልህ ለችሮታው መላሽ የለም፤ ከባሮቹ የሚሻዉን በርሱ ይለይበታል፤ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነው።

On Allah we rely: O our Lord! make us not subject to the persecution of the unjust people: And deliver us by Thy Mercy from those who reject (Thee) (Q10:085-086)