NEME - your only gateway to info. on Islam in Ethiopia and Ethiopian Muslims

O mankind! We created you from male and female, and made you into nations and tribes, so that you may come to know one another. Truly, the most honoured of you in God's sight is the greatest of you in piety. God is All-Knowing, All-Aware. (Qur'an, 49:13)

 
 
 
 Event:- Online Lecture - at 21:00 cet.
WWW NEME
Bilal ul-Habasha
Ethiopian Muslims Community Platform
NOTE: You need to have Unicode Geez font installed on your PC to read the article below. Click here for a PDF version of the text.

በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እና እጅግ በጣም ርህሩህ በሆነው

 

 

በአርሲ የክርስቲያኖች መጨፍጨፍ እና የአንድ ካህን ተማጽኖ በሚል የጀርመን ሬድዮ የአማርኛው ክፍል ያስተላለፈውን ዘገባ በማስመልከት የቀረበ ጥሪ

 

 

ለአንድ ባለታሪክ ህዝብ ከብሄራዊ ችግር የባሰ ሊያሳዝነውሊያስጨንቀውና ሊያስቆጨው የሚችል ነገር አይኖርምበአሁኑ ወቅት አገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ ችግሮች ተወጥራ ትገኛለችይህም ሁኔታ በተለይ ከግንቦት 15 1997ቱ ምርጫ በኋላ ተባብሶ እና ተወሳስቦ ይገኛልታድያ ማንኛዉም ችግር በሰላማዊ ዉይይትና በድሞክራሲያዊ የአሰራር ሂደት መፍትሔ እንዲያገኝ አስካልተደረገ ድረስ ህዝቦች በእርስ በርስ ጦርነት ዉስጥ ሊዘፈቁ ብሎም ሀገሪቱን የማፈራረስ አደጋም ሊያስከትል እንደሚችል መታወቅ ይኖርበታልእንደዚህ በመሳሳሰሉ ችግሮች ዙሪያለእኛ ኢትዮጵያን የመቻቻል አስፋላጊነትንእንደዚሁም በአሉባልታ ላይ የተሞረከዙ ዉንጀላዎችን በተመለከተ ኔትወርካችን በተለያዩ አጋጣሚዎችና መድረኮች ያለዉን አቋም ሲገልጽ ቆይቷል

 

ዛሬም በኅዳር 7 እና 8 1998 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር) በአርሲ በአርሲ የክርስቲያኖች መጨፍጨፍ እና የአንድ ካህን ተማጽኖ በሚል በኖቭምበር 27/29 ዝግጅቱ የጀርመን ሬድዮ የአማርኛው ከፍል ያስተላለፈውን ዝግጅት በማስመልከት ለህብረተሰባችን እንደዚሁም ይመለከታቸዋል ብለን ላመንባቸው ክፍሎች ከታች የቀረበዉን ጥሪ ለማቅረብ ተገደናልለዚህም ያነሳሳን በእዉነት ላይ የተመሰረተ ሚዛናዊ መረጃ እና የመረጃ አሰጣጥ ለአገራችንና ለወገኖቻችን ሰላምና መረጋጋት ብሎም እድገትና ብልጽግና መሠረት ነው የሚል ፅኑ እምነታችን ነውእንኳንስ ከ80 በላይ የሚሆኑ ብሄር እና ብሄረሰቦች ለሚኖሩባትያንኑ ያክል ቋንቋዎች ለሚነገሩባት እና የተለያዩ እምነቶች ለሚተገበሩባት አገራችን ይቅር እና የአንድ ዘር ያላቸውአንድ ቋንቋ ለሚናገሩ እና አንድ እምነት ለሚከተሉ ህዝቦችም አንኳ እውነታ የጎደለዉም ሆነ ሚዛናዊነትን ያልጠበቀ ዘገባ እና የዘገባ አቀራረብ ሊያስከትል የሚችለዉ መዘዝ ቀላል አይሆንምእኛም በጀርመን ድምፅ የአማርኛው ክፍል የተላለፈውን ዘገባ ካዳመጥን እና ካነበብን በሁዋላ ባደረግነው ክትትል ተከሰተ የተባለዉ ጉዳይ ከሞላ ጎደል እዉነታነት ያለዉ ቢሆንም በዘገባው ላይየሀይማኖት ልዪነትእንደመነሻ ተደርጎ መቅረቡናታጣቂ ሙስሊሞች   ክርስቲያኖችን ጨፈጨፉመባሉ ከእዉነታው በእጅጉ የራቀበአቀራረቡ ደግሞ ሚዛናዊነት የጎደለውይልቁንም የአቅራቢዉ ወገንተኝነት ጎልቶ የታየበት ሆኖ አገኝተነዋልከምንም በላይ ያሳዘነን ነገር ቢኖር በህዝቦች መካከል ብጥብጥ እና ጥላቻን የሚያነግስ ዘገባ ሲቀርብ ድርጊቱን ፈፀሙ ከተባሉትና ዉንጀላና ወቀሳም ከቀረበባቸው ከሙስሊሙ ህብረተሰብ በኩል ክስተቱን እና መነሻዉንም ለማጣራት ምንም አይነት ጥረት አለመደረጉ ነውበተለያዪ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ችግሮች መሰቃየቱ አልበቃ ብሎ ይህ አይነቱ ዘገባ እና የዘገባ አቀራረብ ልንወጣው ወደማንችለው ማጥ ሊዘፍቀን ይችላል የሚል ፍርሀት ስላደረብን ጥሪዉን ለማድረግ እንገደዳለንለዚህም

 

ሀ. ኢትዮጵያ ሀገራችን የመጀመሪያ የሙስሊም ስደተኞችን ያስተናገደችበቀያቸዉ እና በህብረተሰባቸው ዉስጥ የእምነት ነፃነት አጥተው ከለላ ለፈለጉ ሙስሊሞች በሯን ከፍታ ተቀብላ ያስተናገደችለእስልምናም እዉቅና በመስጠት እና በመቀበል በዓለም የመጀመሪያ ሀገር መሆኗን ስናስታዉስየዚያኑ ያክል ሀይማኖቱም ሆነ አማኞቹ አሁን ካሉበት ወቅት ለመድረስ የበቁት ከብዙ የመከራና የስቃይ ዘመናትየዜግነት እዉቅናን እስከማጣት የደረሱ የአስተዳደር በደልና ግፎችን በማሳለፍ እንደሆነበሌላ በኩል የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ራሷን ከገዥዎች ጋር በቀጥታ በማቆራኘቷ ችግሩ ሀይማኖታዊ ገጽታ የተላበሰ መሆኑ ሳይካድ

 

ለ. በወራሪ አፄዎች በሙስሊሞችና ከኦርቶዶክስ ክርስትና ዉጭ ባሉ የሌሎች እምነት ተከታይ የሆኑ ኢትዮጵያን ላይ የደረሰው ስቃይና መከራይህም ያስከተለውን የተዛባ የህዝቦች የታሪክ ዘገባ እና ግንኙነቶችን ከግምት በማስገባት

 

ሐ. በሌላ ወገን የክርስቲያኑና የሙስሊሙ እንደዚሁም ከእነዚህ ሁለት እምነቶች ዉጭ ያሉ ሕዝቦች በአንፃራዊ ስምምነቶች ሰላም ኖሯቸው በዚቹ ኢትዮጵያችን ጎን ለጎን ለብዙ ምዕተ-አመታት እንደኖሩ በማስታዎስ

 

የሚከተሉትን ጥሪዎች ለመንግስትለእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤትና ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ተወካዮችለቤተ-ክህነትለመገናኛ ብዙሃን እና ለጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ እናቀርባለን

 

 

1.  ለኢትዮጵያ መንግስት
 

አሁን ተከሰተ ተብሎ የቀረበዉ አይነት ክስተት በተለያዩ ቦታዎች የተከሰተ ወደፊትም በማንኛዉም ቦታና ጊዜ  ሊከሰት የሚችል ሲሆንየተለያዩ ቡድኖችም ሁኔታዉን ከእዉነታዉ በመነጠል ለራሳቸው አኩይ አላማ ሊያዉሉት ሲሞክሩ ታዝበናልይህም በህብረተስባችን ዉስጥ አላስፈላጊን ዉጥረትና የግንኙነት መሻከር ያስከተለበት ሁኔታንም አይተናልስለዚህ እንደዚህ አይነቱን መጥፎ ሂደት መታደግ ይቻል ዘንድመንግስት ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋማትየሀገሪቱ ጎሳዎችና ወኪሎች የተዉጣጣ ሁሉን አቀፍና ከመንግስትም ገለልተኛ የሆነ ሕጋዊ አካል እንዲያቋቁምይህም አካል ችግሮችን ከመከሰታቸዉ በፊት እንዲቀርፍና ከተከሰቱም የመነሻ ምክኒያታቸዉን በማጣራት ለህብረተሰቡ ትክክለኛውን መረጃ እንዲያቀርብ ለመሰል ክስተቶችም ዘላቂ መፍትሔ ያመነጭ ዘንድ ማንኛንም አይነት እገዛ እንዲደረግለት

 

 

2.  ለእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት እና ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ተወካዮች
 

እስልምና በሰላምበመቻቻል እና በመከባበር አብሮ መኖር የሚያስችል ሙሉ የህይወት መመሪያ ነውሙስሊሞችና የሌላ ዕምነት ተከታዮች ጎን ለጎን በሚኖሩባት ሀገራችን ይህ በመቻቻል አብሮ የመኖር ዘይቤ ለኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች አዲስና አስቸጋሪ የሆነ ነገር አንዳልሆነ ግልፅ ነውሆኖም ግን ዕለታዊ ግጭቶችንም ሆነ  በታሪክ ከደረሰው በደል የተነሳ ለሚከሰቱ ችግሮች አስቀድሞ ዘላቂነት ያለው መፍትሄ ለመስጠት ይቻል ዘንድ ሙስሊሙ ህብረሰብ  ተከታታይ እና ቋሚ የሆነ ትምህርት እንደዚሁም እገዛ ሊደረግለት ይገባልለዚህም ገቢራዊነት መጂሊሱ እና ሌሎችም በዳዕዋ ስራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ህብረተሰቡ በራሱ ዉስጥም ይሁን ከሌሎች ጋር ሊያጋጥሙት የሚችሉ ችግሮችና አለመግባባቶችን በዉይይት  ይፈታ ዘንድ አስፈላጊዉን ስልት በመንደፍ እንዲንቀሳቀሱይህንም ለማህበረሰቡ እንዲያስተምሩያለአግባብ በአሉባልታ እና በቂም በቀል የሚወሰድ ማንኛዉም አይነት እርምጃ ከእስልምና አስተምህሮት በእጅጉ የራቀ መሆኑን እንዲያስገነዝቡ

 

 

3.  ለቤተ-ከህነት
 

በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ለሚታየዉ የዘርም ሆነ የሀይማኖት አለመግባባት ህዝቦች ካለፉበት የጭቆናና የስቃይ ዘመን ጋር በቀጥታ ተያያዥነት አለዉ ብለን እናምናለንይህም ሀይማኖታዊ ገፅታ ሊኖረው እንደሚችል ከላይ ጠቆም አድርገን ለማለፍ ሞከርናልየነበረ ቁስል ይድን እና ህዝቦች በውስጣቸው መተማመን ኖሯቸው በመካከላቸዉ የሚከሰቱ ችግሮችን አስቀድመዉ ራሳቸዉ ማስወገድ ይችሉ ዘንድ ቤተ-ክህነት የራሷን አስተዋፆኦ ማድረግ ይገባታልለዚህም ገቢራዊነት ቤተ-ክህነት የአብዛኛዉ ችግር መነሻ ለሆነው ታሪካዊ ክስተት አካል የነበረች መሆኗን ማመን ቅድሚያ ሁኔታ በመሆኑይህንኑ በግልጽ ተቀብላ ለአገርና ለወገን ሰላምና ደህንነት ስትል አስፈላጊዉን እርምጃ እንድትወስድየበኩሏንም ጥረት እንዲታደርግ

 

 

4.  ለመገናኛ ብዙሃን
 

ለአንድ አገርና ህዝብ ሰላምና መረጋጋት ብሎም እድገትና ብልጽግና የመገናኛ ብዙሃን የሚጫወቱት ሚና ይህ ነው ተብሎ የሚገለፅ አይሆንምታድያ ይህ የሚሆነው የሚያቀርቧቸው ዘገባዎች እውነታን የተሞረከዙና  ሚዛናዊነትን የተላበሱ ሲሆኑ በተለይም የህዝቦችን ሰላም እና አብሮ መኖርን የማይረብሹ ከሆነ ብቻ ነውይህ ካልሆነ ግን ዉጤቱ ከላይ የተጠቀሰው ተቃራኒ እንደሚሆን አጠያያቂ አይደለምስለዚህ በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚዘግቡ ሚድያዎች ሁሉ በአሉባልታ ላይ የተመሰረቱ ዘገባዎችን እንዳያቀርቡና ሚዛናዊነትን እንዲጠብቁለአንዱ የአናት ልጅ ለሌላው ደግም የአንጀራ እናት ሆነዉ ከመቅረብ እንዲቆጠቡለአድማጭ ምን አዲስ ነገር ይዘን እንቅረብ ከሚለው ጥረታቸው ጎን ለጎን ይዘው የሚቀርቡት ዘገባ በህብረተሰባቸው መካከል ምን ተፅዕኖ ሊኖረው እንደሚችል አስቀድመው እንዲገመግሙ

 

 

5.  ለመላዉ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ
 

አገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ ካለችበት ዉስብስብ ችግር ልትወጣ የምትችለው በህዝቦቿ ትብብር አንደዚሁም በመካከላቸው በመከባበር እና በመግባባት ላይ የተመሰረተ ሰላም ሲኖር ብቻ ነውአገራችን የተለያዩ ባህሎች ወጎች አና ልማዶች ያሏቸው ብዙ ህዝቦችና ማህበረሰቦች መኖሪያየተለያዩ እምነቶችም የሚተገበሩባት አገር እንደመሆኗ መጠን እነዚህ የተለያዩ ህዝቦችና ማህበረሰቦች በታሪካችን ደረሱብን የሚሏቸው ብሶቶች አሏቸውበተቃራኒው ደግሞ በታሪካችን የነበረንን ቦታ አጣን ወይም ተነፈግን የሚሉም ሊኖሩ ይችላሉታድያ እንደነዚህ አይነቶችን ታሪካዊ ክስተቶች በመጠቀም ህብረተሰቡን መቆሚያ ከማይኖረውና መፍትሄም ከማይገኝለት አጣብቂኝ በመክተት የራሳቸዉን ጠባብ እና መናኛ አጀንዳ ለማራመድ የሚጥሩ ቡድኖችን በተለያዩ አጋጣሚዎች ለማየት ችለናልከዚህም በመነሳት ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ መሰረተ ቢስ ለሆኑ ዘገባዎች ጆሮ እንዳይሰጥአንዱን ህብረተሰብ ወይም እምነት ጠላት ሌላዉን ደግሞ ነብስ-ዓድን አሳቢና ተቆርቋሪ አድርገው ከሚይዙ እና ከሚንቀሳቀሱ ቡድኖችም እራሱን እንዲጠብቅከምንም በላይ የአገራችን ኢትዮጵያ ዉበትና ጌጥ የብዙ ህዝቦችና ማህበረሰቦችባህሎችና ወግ-ልምዶችአምነቶችና ቋንቋዎች ባለቤትነቷ በመሆኑለእነዚህ ልዩና ብርቅየ እሴቶቻችን ልዩ አትኩሮትና ቅድሚያም እንድንሰጥ በማለት ጥሪያችንን እናጠናቅቃለን